Mk corner banner  3

ፍኖተ ማኅበረ ቅዱሳን

  • ማኅበረ ቅዱሳን ከመመስረቱ በፊት የነበረው ተጨባጭ ሁኔታ

    ማኅበረ ቅዱሳን ከመመስረቱ በፊት የነበረው ተጨባጭ ሁኔታ
    ዘመኑ የኮምዩኒዝም ርዕዮተ ዓለምና አስተሳሰብ የሰፈነበት፤ ስመ እግዚአብሔርን መጥራት አስቸጋሪ የሆነበትና ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሔድ እንደ ኋላቀርነት የሚቆጠርበት ዘመን ነበር 1977 ዓ.ም፡፡
    በተለይም በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ /ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች/ በሚገኙ ተማሪዎች ዘንድ ቃለ እግዚአብሔርን በግልጽ መነጋገርም ሆነ መሰማት የማይታሰብበት ወቅት ነው፡፡
    ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይም በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እንዲያስተምሩ ከምዕራባውያኑ ሀገሮች መጥተው የነበሩ ሚሲዮናውያን የኑፋቄ ትምህርታቸውን ያሠራጩ የነበረውም በእነዚሁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው፡፡
    በተለይም በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ /ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች/ በሚገኙ ተማሪዎች ዘንድ ቃለ እግዚአብሔርን በግልጽ መነጋገርም ሆነ መሰማት የማይታሰብበት ወቅት ነው፡፡
  • የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉባኤ

    የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉባኤ
    1977 ዓ/ም ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ጌጡ የኃላሸት በሳምንት ረቡዕ ማታ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት አንሥቶ ለአንድ ሰዓት ያህል ለማስተማር ቅድስት ማርያም ቅጥር ግቢ በመጠላያ ሥር የመጀመሪያው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉባኤ ተጀመረ።
  • ለዪንቨርስቲ ተማሪዎች የመጀመሪያው መንፈሳዊ ጉባኤ በሰንበት ት/ቤት

    ለዪንቨርስቲ ተማሪዎች የመጀመሪያው መንፈሳዊ ጉባኤ በሰንበት ት/ቤት
    ከሚመለከታቸው የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት ሓላፊዎች ጋር በመነጋገር ሰንበት ት/ቤቱ ስር ልዩ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች መርሐ ግብር ለመጀመር ተቻለ። በመጠለያ ሥር የተገመረው ጉባኤም በአዳራሽ ውስጥ ለመካሔድ በቃ።
  • የመጀመሪያው የጽዋ መርሃ ግብር በቅ/ ገብርኤል ስም።

    የመጀመሪያው የጽዋ መርሃ ግብር በቅ/ ገብርኤል ስም።
    የቅዱስ ገብርኤልን መታሰቢያ ለማድረግ የመጀመሪያው የመኝታ ክፍል የጽዋ መርሐ ግብር አንድ ወንድም ከቤተሰቦቹ ባመጣው ጸበል ጸዲቅ እና ተማሪዎች ከመመገቢያ ክፍል ባመጡት ዳቦ እና ውኃ በስድስት ኪሎ ሕንፃ 505 መኝታ ቁጥር 28 ውስጥ ተጀመረ። በስፍራዎ የነበሩት ወንድሞችም የእመቤታችን፣ የቅዱስ ሚካኤልን እና የአቡነ ተ/ሃይማኖትን ጽዋ ለመዘከር በመስማማት የግቢ የጽዋ መርሐ ግብር በዚህ ሁኔታ ተጀመረ። የአራት ኪሎ ወንድሞችም የቅድስት ሥላሴን እና የቅዱስ ጊዮርጊስን ዝክር ማድረግ ጀመሩ።
  • ሰባኪያነ ወንጌል የማፍራት እንቅስቃሴ

    ሰባኪያነ ወንጌል የማፍራት እንቅስቃሴ
    በቀጣዩ ዓመት ከ1979 ዓ.ም እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎቹ በተምሮ ማስተማር ማኅበር አደራሽ ከሚከታተሉት መንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር ጋር ይህ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ በስፋት የሚቀጥልበትን መንገድ ይወያዩ ነበር፡፡ በወቅቱ ትኩረት ተሰጥቶት ውይይት ይደረግበት የነበረው ዐቢይ ጉዳይ ከመካከላቸው ሰባኪ ወንጌል ማፍራት ነበር፡፡
  • በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ሳይንስ ፋኩልቲ እንቅስቃሴ

    በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ሳይንስ ፋኩልቲ እንቅስቃሴ
    እንዲሁም በ1980 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ግቢ ትምህርታቸውን ሊከታተሉ ከገቡት መካከል እስከ ሃምሣ የሚደርሱ ተማሪዎች በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ተሰብስበው ይማሩ ጀመር፡፡
  • የዝዋይ ስልጠና

    የዝዋይ ስልጠና
    ተማሪዎች ለመመረቅ የሚበቁበት ስለነበር ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በዝዋይ የካህናት ማሠልጠን ይፈቀድ እንደሆነ ተጠየቁ። ብፁዕነታቸውም ሲመልሱ ““ተማሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተው አስተምሩኝ ሲሉ በደስታ ነው የምንቀበለው ማረፊያ ቢጠብ ድንኳን ተክለን፣ የምንመገበው ቢያጥር ንፍሮ ቀቅለን እናስተምራችኋለን ስለዚህ ብትመጡ ደስታውን አንችለውም ቤተ ክርስቲያን ኑ ማለት ስገባት እናንተ ከመጣችሁ በሯን ከፍታ ትቀበላችኋለች በደስታ! ይህ ተአምር እና ሰማዕትነትም ነው” ነበር ያሉት።
  • ሁሉንም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ያገናኘ ክስተት

    1982 በአዲስ አበባ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በአንድነት ያገናኘ ልዩ ተአምር። በስድስት ኪሎ፣ በአራት ኪሎ፣ በአምስት ኪሎ፣ በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ፣ በጥቁር አንበሳ እና በሕንፃ ኮሌጅ ይማሩ ለነበሩ ተማሪዎች የስዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ተማሪ ከነበሩ አንድ አባት የእንሰባሰብ ጥሪ ደረሳቸው። በዚህ ምክንያት የየግቢው ተማሪዎች በደረሳቸው ጥሪ ምክንያት በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ ትምህርት አዳራሽ እየተገናኙ መንፈሳዊ ትምህርት መማር ጀመሩ።
  • የመንበረ ፓትሪያርክ ጉባኤ መጀመር

    የመንበረ ፓትሪያርክ ጉባኤ መጀመር
    1982 የስዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ ትምህርት ቤት የተጀመረው መንፈሳዊ ትምህርት እጅግ እየሰፋ ቢሄድም በቦታው ርቀት ምክንያት በተለይ ከኮተቤ ለሚመጡ ወንድሞች እና እህቶች እጅግ ፈታኝ ስለሆነ በጠቅላይ ቤተክህነት ፈቃድ ጉባኤው ወደ መንበረ ፓትሪያርክ አዳራሽ እንዲዛወር ተደረገ።
  • በ1982 ዓ.ም የዝዋይ ገዳም ኮርስ ምረቃ

    በ1982 ዓ.ም የዝዋይ ገዳም ኮርስ ምረቃ
    የመጨረሻዎቹ የአቡነ ጎርጎርዮስ ተማሪዎች ምረቃ ተካሄደ።
  • ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ተለዩ

    ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ተለዩ
    ማንም ያላሰበውና ያልጠበቀው አስደንጋጭ ክስተት ተሰማ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ተለዩ። የብፁእነታቸው ዕረፍት ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን አገልግሎት ያበቃለት እና በጭለማ ውስጥ የተጣለ አስመስሎት ነበር። ይሁን እንጂ የአገልግሎቱ አጀማመር ከሰው አይደለምና በሁሉም ልቡና የአባታችንን ውጥን ከግብ ለማድረስ ከፍተኛ መነሣሣት አሳደረ። ሁሉም በያለበት የተለመደ አገልግሎቱን አጠናክሮ ቀጠለ።
  • ተማሪዎች ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱ ታዘዘ

    በ1983 ዓ.ም በወቅቱ በነበረው መንግሥት በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱ ሲታዘዝ፤ በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጆችና ተቋማት የሚማሩ አሥራ አንድ ሺሕ ያህል ተማሪዎች በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ እንዲገቡ ተደረገ፡፡ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቹ ግቢዎች ተጀምሮ ቀስ በቀስ የተስፋፋው መንፈሳዊ እንቅስቃሴም የበለጠ የሰፋበትና የተጠናከረበት ጊዜ ሆነ፡፡
  • በቅዱስ ሚካኤል ስም የጽዋ ማኅበር ተቋቋመ

    በቅዱስ ሚካኤል ስም የጽዋ ማኅበር ተቋቋመ
    ቀድሞ በብላቴ በነበሩበት ወቅት በቅዱስ ሚካኤል ስም ማኅበር በማቋቋም ለመሰባሰብ ብፅዓት ገብተው የነበሩት የየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በአዲስ አበባ ግቢ ገብርኤል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ በተደረገ ስብሰባ ማኅበረ ሚካኤልን መሥርተው ደንቡን በማጽደቅና አመራሩን በመመ ረጥ ወደ የመጡበት ተመልሰዋል።
  • የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በካምፕ የተከበረበት

     የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በካምፕ የተከበረበት
    ግንቦት 1/1983 ለመጀመሪያ ጊዜ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በካምፕ የተከበረበት። ይህ በዓል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እስከመተላለፍ ደርሶ ነበር።
  • የዝዋይ ደቀ መዛሙርት ማኅበር ተቋቋመ

    የዝዋይ ደቀ መዛሙርት ማኅበር ተቋቋመ
    በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሀገረ ስብከት ላይ በጊዜያዊነት ተመድበው የነበሩት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ጅምር ከዳሙ ማኅበረሰብ እና ከደቀመዛሙርቱ ጠንቅቀው በመረዳታቸው በጉዳዩ ላይ እና በአገልግሎቱ ቀጣይነት ላይ ለመወያየት እንዲቻል ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ተምረው ከገዳሙ ሠልጥነው የወጡትን ደቀ ማዙሙርት ሁሉ ለብፁዕነታቸው ሙት ዓመት መታሰቢያ ወደ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እንዲሰበሰቡ ጥብቅ ጥሪ አደረጉ። በጥሪውም መሰረት ከብዙ ውይይት በኋላ አገልግሎቱን የበለጠ ለማጠናከር የዝዋይ ደቀ መዛሙርት ማኅበር ተቋቋመ።
  • በቅድስት ድንግል ማርያም ስም የጽዋ ማኅበር ተቋቋመ።

    በቅድስት ድንግል ማርያም ስም የጽዋ ማኅበር ተቋቋመ።
    የቅድስት ማርያም የጽዋ ማኅበር፣ የዝዋይ ደቀመዛሙርት ማኅበር፣ የጥቁር አንበሳ ተማሪዎች የሥላሴ ማኅበር፣ በወቅቱ ስላቴ ዘምተወ የነበሩት ተማሪዎች ማኅበረ ሚካኤል ወደ አንድ ጠንካራ ማኅበር ማጠቃለለ እንደሚገባ ከስምምነት ላይ ተደረሰ። በብፁዕ አቡነ ገብርኤል መኖሪያ ቤት በተደረገ ስብሰባም በአማራጭነት ከቀረቡት ማኅበረ ሐዋርያት፣ ማኅበረ አርድዕት እና ማኅበረ ቅዱሳን መካከል ከላይ የተጠቀሱት ማኅበራትም ሁሉም የቅዱሳን መታሰቢያ በመሆናቸው የማኅበሩ ስያሜ “ማኅበረ ቅዱሳን” እንዲሆንን በብፁዕ አቡነ ገብርኤል የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቷል።
  • የማኅበረ ቅዱሳን መመስረት

    የማኅበረ ቅዱሳን መመስረት
    በጥር ወር 1984 ዓ.ም በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው «ማኅበረ ሚካኤል» የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ አጽድቆ አመራሩንም መርጧል፡፡ ሆኖም በቅዱሳኑ ስም ማኅበር መሥርተው የተሰባሰቡት አባላት፤ «ዓላማቸው፣ አገልግሎታቸውም ሆነ ታሪካቸው አንድ ነው፡፡ ለምን አንድ ስያሜ ይዘው በአንድነት አይንቀሳቀሱም?» የሚል ሐሳብ በውስጣቸው እየተነሣ በተለያዩ አጋጣሚዎች በጉዳዩ ሲወያዩበት ቆይቷል፡፡
    በዚህ ዓይነት ማኅበረ ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተክርስቲያኒቷ መዋቅር ዕውቅና አግኝቶ ግንቦት 2 ቀን 1984 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር መደራጀቱ ይፋ ሆነ፡፡
  • በሐመር መጽሄት አማካኝነት ማኅበሩ በብዕር ድምጽ የቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ማሰማት ጀመረ

    በሐመር መጽሄት አማካኝነት ማኅበሩ በብዕር ድምጽ የቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ማሰማት ጀመረ
    1985 ዓ/ም በሐመር መጽሄት አማካኝነት ማኅበሩ በብዕር ድምጽ የቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ማሰማት ጀመረ። ይህ ክስተት በያህማኖት ላይ የተሰነዘረው የመናፍቃን ቅሰጣ ለመመከትና ይምህርተ ወንጌልን ለማስፋት ዓይነተኛ አስተዋጽኦ ነበረው። ስምዐ ጽድቅም ከሐመር ባልተናነሰ ሁኔታ ዜና ዘገባዎችንና ትምህርታዊ ጽሑፎችን ይዛ ብቅ በማለቱ የማኅበሩን አገልግሎት አንድ ጋት ወደፊት ከመራመዱም በላይ ምእመናን ስለያህማኖታቸውና ስለበተ ክርስቲያናቸው በቅርች እንዲያውቁና እንዲረዱ የነበረው አስተዋጽዎ ከፍተኛ ነበር።
  • የማኅበሩ የምስረታ በዓል እና የግንቦት ልደታ

    የማኅበሩ የምስረታ በዓል እና የግንቦት ልደታ የደመቀ በዓል በተጨማሪ የማኅበሩ አመታዊ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉም አባላቱ በተገኙበት በታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ተካሄደ። የማኅበሩ የመተዳደሪያ ደንብ የጸደቀው በዚህ ጉባኤ ላይ ነው።
  • የመጀመሪያው የዩንቨርስቲ ተማሪዎች መንፈሳዊ የምረቃ መጽሔት ተዘጋጀ።

    1986 ዓ/ም የመጀመሪያው የዩንቨርስቲ ተማሪዎች መንፈሳዊ የምረቃ መጽሔት ተዘጋጀ።
  • ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከመቶ ሺህ በላይ ታተመ

    ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከመቶ ሺህ በላይ ታተመ
    በዚህ አመት 110,000 ኮፒ ታትሞ ለምእመናን ተሰራጨ።
  • የሐመር መጽሄት ህትመት ብዛት ከመቶ ሺህ በላይ ሆነ

    የሐመር መጽሄት ህትመት ብዛት ከመቶ ሺህ በላይ ሆነ
    በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሐመር መጽሄት ህትመት ከመቶ ሺህ በላይ ሆኖ 146,000 ታትሞ ለምእመናን ተሰራጨ።
  • የአሜሪካ ማዕከል ተቋቋመ

    በሰሜን አሜሪካ ያለውን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለማገዝ እና በሃገር ቤት ያለውንም ለመደገፍ በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል ተቋቋመ።
  • የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል

    “ትውልድን የሚተካ ይውልድ በተሻለ ጥራት እናፈራለን” የሚል ዓላማ ይዞ የተነሣው ይምህርት ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን ከፍቶ በድምሩ ከሦስት ሺህ አምስት መቶ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።
  • የነዋያተ ቅድሳትና የሥጦታ ማምረቻና ማከፋፈያ ተቋቋመ

    የነዋያተ ቅድሳትና የሥጦታ ማምረቻና ማከፋፈያ ተቋቋመ
    ማምረቻው አገልግሎቱን የጀመረው በሁለት መደበኛ አገልጋዮች፣ በሁለት የስፌት መኪናና በአንድ የልብስ ካውያ ነበር።
  • Period: to

    ተተኪ ሰባኪያንን ማፍራት

    ሁለት መቶ ሠላሳ ሦስት በኦሮምኛ ቋንቋ፣ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ አራት በአማርኛ ቋንቋ ተተኪ ሰባክያንን አሰልጥኗል።
  • ልማት ተቋማት አስተዳደር በአዲስ መልክ ተቋቋመ

    ከቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓትና ትውፊት ጋር የማይጋጩ፣ ጠቃሚና ማሳያ የሆኑ ምርቶችንንና አገልግሎቶችን ለኅብረተሰቡ በስፋት አቅርቦ አስተማማኝ ገቢ በማግኘት የማኅበሩን አገልግሎት በዘላቂነት መደጎም ርዕዩ እና ዓላማው ሲሆን፣ ተልዕኮውም የሣይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ጠንካራ ውስጣዊ አደረጃጀትና ቁጥጥር በመዘርጋት ነባር ተቋማትን ማጠናከር እንዲሁም አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን በመክፈት ውጤታማነትን ማሳደግ ነው።
  • ኦዲዮ ቪዥዋልና ሥነ-ጥበባት ሥራዎች ማዕከል ተቋቋመ

    ኦዲዮ ቪዥዋልና  ሥነ-ጥበባት ሥራዎች ማዕከል ተቋቋመ
    ማዕከሉ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል ጥቂቶቹ:መዝሙሮችን፣ ስብከቶችን፣ መንፈሳዊ ፊልሞችን ትረካዎችን፣ ማስታወቁያዎችን፣ ዘጋቢ ፊልሞችን፣ መንፈሳዊ ጉዞዎችን እና ሌሎችንም ስራዎች በጥራት በመቅረጽና በኮምፒዩተር በማቀናበር በቴፕ ና በሲዲና በሺዲዮ ካሴቶች ያቀርባል።
  • የጽ/ቤት ግንባታ እንዲጀመር ተወሰነ

    የጽ/ቤት ግንባታ እንዲጀመር ተወሰነ
    ነሐሴ 1994 ዓ/ም የተደረገው 5ኛው የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ በአንድ ድምጽ የጽ/ቤት ግንባታው እንዲጀመር ሰወስን በወቅቱ ማኅበሩ አገልግሎቱን የፈጽምበት ከነበረው ጥቂት ገንዘብ በቀር በካዝና የተቀመጠ ምንም ገንዘብ አልነበረውም። የማኅበሩ አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን በአንድ ዓመት እንዲከፍሉ፣ ግቢ ጉባኤያትም ባላቸው የተማሪዎች ቁጥር መሠረት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጉባኤው የውሳኔ ሀሳብ አቀረበ።
  • Period: to

    ቅዱሳት መጻሕፍት ህተመት

    የልማት ተቋማት አስተዳደር በዓይነት ከ150 በላይ የሚሆኑ በተለያየ ርዕስ ዙሪያ የተጻፉ ቅዱሳት መጻሕፍት አዘጋጅቶና አሳትሞ ለምእመናን አሰራጭቷል።
  • የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ማስተማሪያ ሥርዓተ ትምህርት አዘጋጅቶ ጥቅም ላይ አዋለ

    ተከታታይና ወጥነት ያልነበረውን የግቢ ጉባኤያት ትምህርት እንዲስተካከል ማኅበሩ ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾ ሃያ የመማሪያ መጻሕፍት አዘጋጅቶ በመላ ሀገሪቱ ባሉ ከ350 በሚበልጡ ግቢ ጉባኤያት ተግባራዊ አድርጓል።
  • በተለያየ ቋንቋ የሚሰብኩ ደቀ መዛሙርትን ማፍራት

    በተለያየ ቋንቋ የሚሰብኩ ደቀ መዛሙርትን ማፍራት
    ጠረፋማና ክርስታ ና ካልተስፋፋባቸው አካባቢዎች በየጊዜው ተተኪ ሰባክያንን እየመለመለ አዲስ አበባ በማምጣት ሰባክያንን አሰልጥኖ በየቋንቋቸው ወንጌልን ለወገኖቻቸው እንዲያደርሱ አድርጓል።
  • 1998 በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ተቋም ተቋቋመ

    1998 በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ተቋም ተቋቋመ
    1998 በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ተቋም ተቋቋመ
  • ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ታተመ

    ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ታተመ
    በዚህ ዓመት 228,000 ስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ ታትሞ ለምእመናን ቀረበ።
  • ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱሳን መካናት ዘርፍ

    ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱሳን መካናት ዘርፍ
    2000 ዓ/ም ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱሳን መካናት ዘርፍ ባለው አገልግሎት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመተግበር ከጊዜያዊ እርዳታ ወደ ቋሚና ዘላቂ የሆነ ፕሮጀክት ገዳማቱ እንዲሸጋገሩ አስችሏል።
  • ሐመር መጽሄት ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ታተመ

    ሐመር መጽሄት ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ታተመ
    በዚህ ዓመት 246,834 ስምዓ ጽድቅ ታትሞ ለምእመናን ቀረበ።
  • የ10 ዓመቱ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሃ ግብር ተጀመረ

    የ10 ዓመቱ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሃ ግብር ተጀመረ
    የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ሓላፊነት ለመወጣት ባለፉት 20 ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፤ እያደረገም ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም የቤተክርስቲያን አባላት ባሳተፈ እና እያንዳንዱ ምዕመን የድርሻቸውን እንዲወጡ በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ፤ ስብከተ ወንጌል አገልግሎት ባልተስፋፋባቸው ገጠርና ጠረፋማ ቦታዎች፤ አኅዛብና መናፍቃን በበዛባቸው አካከባቢዎች ወንጌልን ለማዳረስ የአሥር ዓመት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ማስፋፊያ ኘሮግራም በመቅረጽ በግንቦት 19/2002 ዓ.ም. አገልግሎቱን ጀምሯ::
  • የሕዝብ ጉባኤያትን ማዘጋጀት

    የሕዝብ ጉባኤያትን ማዘጋጀት
    ባለፈው በ2003 ዓ/ም እንዲካሄዱ ከታሰቡት ከሃያው/20/ ሀገረ ስብከት መቀመጫ ከተሞች የሕዝብ ጉባኤያት አስራ ስድስቱ/16/ ማለትም
    • በጅማ ሀ/ስብከት- ጅማ ከተማ፣
    • ጋሞ ጎፋ ሀ/ስብከት በአርባ ምንጭ ከተማ ፣
    • አፋር ሀ/ስብከት-አዋሽ ሰባት ከተማ፣
    • ሐዲያና ስልጤ ሀ/ስብከት- ሆሳዕና ከተማ ፣
    • ድሬደዋ ሀ/ስብከት- ድሬደዋ ከተማ፣
    • ኦጋዴን እና ሶማሌ ሀ/ስብከት -ጅጅጋ ከተማ ፣
    • ከንባታ አላባና ጠንባሮ ሀ/ስብከት- ዱራሜ ከተማ፣
    • ምስራቅ ሐረርጌ ሀ/ስብከት - ሐረር ከተማ፣
    • ሸካ ቤንች ማጂ ሀ/ስብከት - ሚዛን ተፈሪ ከተማ ፣
    • ከፋ ሀ/ስብከት - ቦንጋ ከተማ እና
    • ደቡብ ኦሞ ሀ/ስብከት - ጂንካ ከተማ የሕዝብ ጉባኤያት ተደርገዋል፡፡
    በዚህም አገልግሎት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት፣ የሰዋሰው
  • 60 የህዝብ ጉባኤያት ተካሄዱ።

    60 የህዝብ ጉባኤያት ተካሄዱ።
    በ2004 ግማሽ ዓመት ተይዘው ከነበሩ እቅዶች መካከል 6 ሐዋርያዊ ጉዞዎችን እና 75 የህዝብ ጉባኤያትን ለማካሄድ ታቅዶ የነበረ ሲሆን በወላይታ፣ በባሌ ሮቤ፣ በቦንጋ፣ በዱራሜ፣ በሐረር ፣በምዕራብ ሐረራጌ ሐዋርያዊ ጉዘዎች እና ሌሎች ሀገረ ስብከቶችን ጨምሮ 60 የህዝብ ጉባኤያት ተካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሮችም መዝመራት በተለያዩ መምህራን ሰበከተወንጌል የተከናወነ ሲሆን ምእመናን በሠጡት አስተያዬት ይህ መረሃ ግብር ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
  • ገዳማትና አድባራትን ከመደገፍ አንጻር

    ገዳማትና አድባራትን ከመደገፍ አንጻር
    ማኅበሩ ከአብነት ት/ቤቶች በተጨማሪ ችግር ላለባቸው አድባራትና ገዳማት ጊዜያዊ ርዳታ በማድረግ እና ዘላቂ መፍትሔዎችን በማመቻቸት የገዳማቱንና አድባራቱን ችግር በመጠኑም ቢሆን እየፈታ ይገኛል፡፡ በጊዜያዊ ርዳታ የተለያዩ የመባዕ /ጧፍ፣ ነዕጣን፣ ዘቢብና ሻማ/፣ የተለያዩ ንዋየ ቅድሳት /ልብሰ ተክህኖ፣ መጎናጸፊያ ወዘተ/፣ የዘወትር ልብስ፣ የምግብ እህልና ሌሎችን ርዳታዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በዓመት በአማካይ ለሠላሳ ቅዱሳት መካናት የልብሰ ተክህኖ ድጋፍ፣ ለሁለት መቶ ቅዱሳት መካናት የመባዕ፣ እንዲሁም የምግብ፣ የአልባሳት እና ለሌሎች ድጋፎች በዓመት እስከ ዘጠና ሺሕ ብር ወጪ ያደርግላቸውል፡፡ በ1995 ዓ.ም በሁለት የአብነት መምህራን የተጀ መረው ድጎማ ዛሬ ቁጥሩን ከፍ በማድረግ ስልሳ ለሚሆኑ ለተመረጡ አብነት ት/ቤቶች ድጎማ ያደርጋል።
  • ድምጸ ተዋህዶ የሬድዮ አገልግሎት ተጀመረ

    ድምጸ ተዋህዶ የሬድዮ አገልግሎት ተጀመረ
  • ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ

    ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ
    ማኅበሩ በተለያዩ ሰው ሠራሽም ሆኑ ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች ችግር ከደረሰባቸው ገዳማትና አድባራት ባሻገር በችግር ውስጥ ያሉ ምእመናንንም በመታደግ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ በመስከረምና ጥቅምት 1999 ዓ.ም በአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ጉዳት ለደረሰባቸው የጅማ፣ ኢሉባቦር እና የምዕራብ ወለጋ አህጉረ ስብከት ምእመናንን እና አባላትን በማስተባበር የመልሶ ማቋቋም ሥራ ሠርቷል፡፡ በዚህም ለተፈናቀሉት የኅብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ርዳታ ጤፍ፣ በቆሎና ማሽላበጠቅላላው ለዘጠኝ መቶ ሃያ ስድስት አባወራ አምስት መቶ አሥራ አንድ ኩንታል ገዝቶ አከፋፍሏል፡፡ በኢሊባቦር ለተቃጠሉ ቤቶችም መልሶ ግንባታ ለሃምሳ አንድ አባወራ ለእያንዳንዳቸው አርባ ቆርቆሮና ሚስማር ሰጥቷል፡፡
  • ኤች አይ ቪ/ኤድስን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ

    ማኅበሩ ኤች አይ ቪ/ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድም ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን እየሠራ ይገኛል፡፡ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ እያስጨበጠ ይገኛል፡፡ የቤተ ክርስቲ ያን ትምህርትን መሠረት ያደረጉ የመከላከያ እና የመቆጣጠሪያ ዘዴዎች ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ከስዊድን የሕፃናት አድን ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ፣ ከአክሽን ኤይድ እና ቪ.ኤስ.ኦ. ከተባሉ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተለያዩ ሥራዎችንም ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ከተሠሩትም ሥራዎች መካከል ተከታታይ ጽሑፎች በ«ስምዐ ጽድቅ» ጋዜጣ እና «ሐመር» መጽሔት በማውጣት፣ አርባ የሚሆኑ ፀረ ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ክበባትን ማቋቋም፣ ለዘጠኝ መቶ ዘጠና ሦስት ካህናትና ካውንስለሮች ሥልጠና በመስጠት፣ ለስድስት መቶ አምስት የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችና ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች የአቻ ለ
  • የሙያ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያናችን

    የሙያ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያናችን
    ከ1995 ዓ.ም ወዲህ ከተሠሩትና በዋነኛነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ለስምንት የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክቶች ዲዛይንና የዋጋ ዝርዝር፣ ለሰባ አምስት አብያተ ክርስቲያናት ሕንፃ ዲዛይን፣ ከሠላሳ በላይ ለሆኑ አብያተ ክርስቲያናት የጥገና ዲዛይን፤ እንዲሁም ከሠላሳ በላይ ለተለያዩ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ዲዛይኖችን ሠርተው አስረክበዋል፡፡
  • የቴሌሺዥን አገልግሎት ጀመረ

    የቴሌሺዥን አገልግሎት ጀመረ