Background

የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት የተጣሰባቸውን ክስተቶች

  • (3/1/1985 E.C) - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ በመንግሰት የተከለከለ የአካል ጉዳት የደረሰበት

    (3/1/1985 E.C) - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ በመንግሰት የተከለከለ የአካል ጉዳት የደረሰበት
  • (7/12/1989 - E.C) የአማራ ክልል የመሬት ድልድልን አስመልክቶ የተቃውሞ ሰልፍ ሙከራ ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታስረዋል፡፡ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

  • (7/1/1994 -E.C) ነቀምት 2ተኛ ደረጃ ተማሪዎች የኦሮሚያን የደን መቃጠልን አስመልክቶ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ 102 ሰዎች ታረዋል

    14 በድጋሚ በአስተባባሪነት ታስረዋል
  • (7/1/1994 -E.C) ምስራቅ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ኦህዴድን እና መንግስትን በመቃወም በትምህርት መውጫ ሰአት ላይ ያደረጉት የሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ 3 ተማሪዎች ሞት እና የ5 ተማሪዎች መቁሰል ተጠናቆዋል

  • (7/1/1994 -E.C) አምቦ ከተማ ለኦህዴድ የምስረታ በአልን አስመልክቶ የተጠሩ መምህራን እና ተማሪዎች ወደ ስታዲየም ሲሄዱ ሃሳባቸውን ቀይረው ተቃውሞ ማሰማት በመጀመራቸው ፓሊሶች ሰልፉን ለመበተን ባደረጉት ሙከራ 1 ሰው ሞቶ 1 ሰው ቆስሎ 4 ተማሪዎች ታስረው ሰልፉ ተበትኖአል፡

  • (7/20/1994 - EC) ምእራብ ሸዋ ዞን ጌዶ ከተማ የአምቦን ከተማ ሰላማዊ ሰልፍን ተከትሎ ጌዶ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ፓሊስ ተኩስ ከፍቶ 1 ሰው ሲሞት 4 የአካል ጉዳት ደርሶአል፡፡

  • (In 1995- E.C) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ግን ምደባ ያልደረሳቸው ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቀው በፍቃድ መስጫ ክፍሉ ተከልክለዋል፡፡

  • አለም አቀፍ የመምህራንን ቀን አስመልክቶ ኢመማ መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ ለሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ አካል አሳውቆ ያቀረበው ማስረጃ የድርጅቱን ህጋዊ ሰውነት አያሳይም በሚል የተከለከለ

  • (4/25/1996 - E.C) ሜጫና ቱለማ ልማትና መረዳጃ ማህበር የኦሮሚያ ዋና ከተማ ከአ.አ ወደ አዳማ መዞሩን በመቃወም ታህሳስ 25/1996 የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አድርጎ ያለምንም በቂ ምክንያት የተከለከለ፡፡ መከልከሉን ያልሰሙ ጥቂት አባላት መስቀል አደባባይ በመገኘታቸው በፌደራል ፓሊስ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡

  • (5/9/1996 - E.C) አ.አ ዮኒቨርሲቲ የኦሮሞ ተማሪዎች በቅጥር ጊቢያቸው ውስጥ ተቃውሞ የማሰማት ጥረት በፌደራል ፓሊስ የተከለከለ

  • (6/22/1996 EC) ምእራብ ሸዋ ዞን ጥቁር ኢንጪን ወረዳ -ኢንጪን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተቃውሞ ስብሰባና ሰልፍ የማድረግ ጥረት በፖሊስ የተበተን

    1 ተማሪ ሞትዋል
    1 ተማሪ ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል
    3 ተማሪዎች ለተወሰነ ግዜ ታስረዋል
    4. ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙከራ
    14 የታሰሩ ተማሪዎች
    ከባድ ድብደባ አና ስብሰባውን የመበተን ተኩስ ነበር
  • (6/22/1996 - E.C) ምእራብ ሸዋ ዞን ጥቁር ኢንጪን ወረዳ -ኢንጪን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተቃውሞ ስብሰባና ሰልፍ የማድረግ ጥረት በፖሊስ የተበተን

    1 ተማሪ ሞትዋል
    1 ተማሪ ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል
    3 ተማሪዎች ለተወሰነ ግዜ ታስረዋል
  • (6/25/1996 - E.C) በአምቦ አንደኛ ደረጃና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በቅጥር ጊቢያቸው ተነስተው ወደ ከተማ ለተቃውሞ ሰልፍ ያረረጉት ጥረት በፓሊስ ተበትኖአል፡፡ ተቃውሞአቸው ቀደም ብሎ የነበረውን የአአ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቃውሞ ተከተሎ ነው፡፡

    የደረሰ ጉዳት-የተማሪዎች ድብደባ እና 38 ተማሪዎች እስራት
  • (6/30/1996 - E.C) ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙከራ

    14 የታሰሩ ተማሪዎች
    ከባድ ድብደባ አና ስብሰባውን የመበተን ተኩስ ነበር
  • ተሰብስበው ውይይት ሲያደርጉ የነበሩ የአለማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመከላከያ ፖሊስ መሰብሰብ አይቻልም ተብለው በሃይል ሲበተኑ 5 ተማሪዎች ተስረዋል፡፡

  • ጅማ ኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ተቋሟቸውን ለመግለጽ ቅጥር ጊቢያቸው ውስጥ ተሰብስበው ብዙ ተማሪዎች በፓሊስ ድብደባ ሲደርስባቸው 18 ተማዎች ታስረዋል፡፡

  • ተቃውሞ ሊያሰሙ አደባባይ የወጡ ዜጎች ላይ በደረሰ ጥቃት - ኢሰመጉ ያጣራው

    32 ሰው ጎዳና ላይ ተገድሎአል
    62 ሰው በከባድና ቀላል የአካል ጉዳትና ቁስለት ደርሶበታል
    304 ሰዎች በእለቱ በጅምላ የታሰሩና ማስረጃ የተገኘላቸው ናቸው
    28 ሰዎች በወቅቱ ተይዘው የደረሱበት ያልታወቀ
    54 ሰዎች ዘግይቶ የታሰሩ
    12 ሰዋች ያለፍርድ የተገደሉ
    (ይህ መረጃ ኢሰመጉ ብቻ የተጣራ ነው)